በዲሊቨሮሎጂ ዩኒት በዲሊቨሮሎጂ ዩኒት

በዲሊቨሮሎጂ ዩኒት እቅድ መሰረት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን ጀምሮ በየደረጃው ያለ አመራር፣ ባለድርሻ አካላትና የከተማችን ነዋሪው ህብረተሰብ አካባቢያቸውን ወር በገባ በ11ኛው ቀን የማጽዳት ፕሮግራም እንደሚጀምር ኤጀንሲው አስታወቀ፡፡

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀሳብ አፍላቂነት የከተማዋን የአካባቢ የጽዳት ችግሮች ጊዜ የለኝም በሚል አስተሳሰብና ዘላቂነት ያለው የአካባቢ ጽዳት ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ወርሃዊ የአካባቢ ጽዳት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስተራችን ጀምሮ በየደረጃው ያለ አመራር፣ ባለድርሻ አካላትና የከተማችን ነዋሪው ህብረተሰብ ልዩ የሆኑ ቦታዎችን በመረከብ አካባቢያቸውን በኃላፊነትና በዘላቂነት በሕዝብ ንቅናቄ የማጽዳቱንና የማልማቱን ስራው ወር በገባ በ11ኛው ቀን  ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ይፋ እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ማስረሻው አስናቀው በዲሊቨሮሎጂ ዩኒት እቅድ የሳምንት አፈጻጸምና ግምገማ ውይይት ላይ ገልጸዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪውን ህብረተሰብ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አሰባሰብ ግንዛቤውን ለማሻሻል በተመረጡ የሚዲያ ተቋማት የጀመርነውን ስራዎች በቀጣይ በሁሉም ሚዲያ በመጠቀም የተለያዩ ስፖቶችን፣ ዶክመንተሪ ፊልሞችን እና ፕሮግራሞችን ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ባሕል ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል የኤጀንሲው  ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ማስረሻው   አክለው ተናግረዋል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይርጋለም በርሃኔ በበኩላቸው በዲሊቨሮሎጂ ዩኒት እቅድ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ 814 ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ መስቀመጫዎችን ወደ  85 በማምጣት ደረጃቸውን፣ ጥራታቸውን እና ስታንዳርዳቸውን በጠበቀ መልኩ እያንዳንዳቸው 500 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ የሚገነቡ መሆናቸውን ገልጸው፤ በቦታ ዝግጅት ላይ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በስተቀር ሌሎቹ ክፍለ ከተሞች  ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ መስቀመጫ ቦታዎችን መርጠው ባስገቡት መሰረት አብዛኛዎቹ ቦታዎች ተቀባይነትን አገኝተዋል ብለዋል፡፡

 

 

....

ፈጣን የመረጃ ምንጮች ፈጣን የመረጃ ምንጮች

ተዛማጅ ድህረ-ገጾች ተዛማጅ ድህረ-ገጾች